Saturday, 27 May 2017

UNION OF TIGREANS IN BAHIR DAR

UNION OF TIGREANS IN BAHIR DAR
               ማሕበር ተጋሩ ባህር ዳር (...)


P.O.BOX 73736
ባህር DAR 
             20056
BDUJOCO@gmail.com


Tel. (202) 862-4367
Fax. (202) 265-8703
www.atbd  .org
የግንቦት 20 የድል ቀንን በማስመልከት ከትግራይ ተወላጆች ማሕበር በባህር ዳር ከተማ 
                                                                   የተሰጠ የድጋፍ መልዕክት
 የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረስቦች እና ህዝቦች፡
በመጀመሪያ ለዚች ለተከበረች የመላ ኢትዮጵያዊያን የድል ቀን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። ይህችን ቀን ስናከብር፣ ለዘመናት በኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔርሰቦች እና ህዝቦች ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረውን የመደብ እና የብሔር ጭቆና ቀንበር እንዲሁም የድህነት እና የኋላ ቀርነት ዘብ የነበረውን ስርዓት ለመገርሰስ ውድ ህይወታቸውን የከፈሉ ኢትዮጵያዊያንን በማሰብ፣ በማክበር እና በመዘከር ነው።
17 ዓመታት የተካሄደው መራራ እና የተራዘመ ትግል በመላ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረስቦች እና ህዝቦች
ተሳትፎ ወታደራዊው ጨቋኙ የደርግ ስርዓት ተወግዶ በምትኩ ልምታዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ሕገ
መንግስታዊ ስርዓት ከተተከለ ይኸው ድፍን ሩብ ክፍለ ዘመን ተቆጥሯል። ኢትዮጵያ ሀገራችን ዜጎቿ የሰላም
አየር ርቋቸው ለዘመናት ለስደት እና የመከራ ተዳርገው የነበሩበት ዘመን አብቅቶ፤ አሁን በአንድነት
ተፈቃቅረው እና ተፈቃቅደው የሚኖሩባት አዲስቷ ኢትዮጵያ ለመመስረት የበቁት ከብዙ መስዋእት እና
ውጣ ውረድ በኋላ መኾኑን በመገንዘብ፣ ማሕበራችን የትግራይ ተወላጆች ማሕበር በባህር ባር ከተማ  ይህ
ሂደት ቀጣይ እንዲኾን እና ተጠናክሮ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የሁሉም ዜጋ ድርሻ ነው ብሎ ያምናል።
ማሕበራችን ልክ በትጥቅ ትግሉ ዘመን ከጭቁን ህዝቦች ጋር በመተባበር የህዝቦች ተጋድሎ ፍሬ እንዲያፈራና
በድል እንዲጠናቀቅ ከንብረት እስከ ህይወት መስዋእት በመክፈል ለትግሉ ድጋፍ እንዳደረገው፣ አሁንም
በሰላም፣ በልማት እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ባለፉት 26 ዓመታት ሀገራችን በክፍለ አህጉራዊ እና በአህጉራዊ መድረኮች ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ የልማት እና የመረጋጋት ተምሳሌት ኾና እንድትገኝ አስተዋጽኦ ላደረጉ መላ የኢትዮጵያ ህዝቦች ታላቅ ክብር አለን። እኛም በዚሁ ሂደት የበኩላችን አስተዋጽኦ በማበርከታችን ኩራት ይሰማናል።
በዚህ አጋጣሚ ማሕበራችን የተመሰረተበት 43 ዓመት በመጪው ኦገስት 2018 እንደሚያከብር
እየገለጽን፣ ልክ እንደ ካሁን በፊቱ፣ አስከፊውን ስርዓት ለማስወገድ 17 ዓመታት የከፈልነው መስዋእት
እየዘከርን፤ እንዲሁም ባለፉት 26 ዓመታት በልማት፣ ሰላም እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የነበረን
አስተዋጽኦ ይበልጥ አጠናክረን በመቀጠል፤ ከሌሎች በዳያስፖራ የሚገኙ ህዝባዊ ማሕበሮች ጋር ተባብረን
በመስራት ሀገራችን የተያያዘቸው ፈጣን የልማት ጎዳና እና ሁለተኛውን የዕድገት ትራንስፎርሜሽን እቅድ
እውን ለማድረግ በሙሉ ልብ እንደምንረባረብ በዚች የተከበረች የኢትዮጵያዊያን የድል ቀን ቃል ስንገባ
ደስታችን ወደር የለዉም።
ዘለአለማዊ ዝክር እና ክብር ለትግሉ ሰማእታት!! ግንቦት 20/ 2008 /
የትግራይ ተወላጆች ማሕበር በባህር ዳ ከተማ 
                            ማእከላዊ ጽ/ቤት 
ፊትለፊት አዲስ አምባ ሆቴል 

No comments:

Post a Comment

TEKLEHAIMANOT JOCO

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተያይዞ ዛሬ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ። በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተመልክቷል። የዩኒቨርስቲው ...