Tuesday 6 March 2018

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተያይዞ ዛሬ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።
በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተመልክቷል።
የዩኒቨርስቲው ኮሙዩኒኬሽንና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተሻለ ተገኔ እንደገለጹት፥ እሳቱ የተነሳው ቀን ሰባት ሰዓት አካባቢ በተማሪዎች ማደሪያ አንድ ብሎክ ውስጥ ነው።
በቃጠሎው በብሎኩ የተወሰኑ ክፍሎች የተማሪዎች አልጋ ፍራሾችና ሌላም ቁሳቁሶች ወድመዋል።
እንዲሁም የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ህንፃ ውስጥ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒተሮችና ተጓዳኝ መገልገያዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና የሶዶ ከተማ ፖሊስ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ጋር በመሆን ባደረጉት የጋራ ርብርብ ቃጠሎ ሳይስፋፋ መቆጣጠር መቻሉንም አመልክተዋል።
ምንጭ፦ኢዜአ

TEKLEHAIMANOT JOCO

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተያይዞ ዛሬ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ። በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተመልክቷል። የዩኒቨርስቲው ...