Friday 16 June 2017

ዘመን_ተሻጋሪ_የባለ_ራእይ_ትምቢታዊ_ንግግር!

#ዘመን_ተሻጋሪ_የባለ_ራእይ_ትምቢታዊ_ንግግር!

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ልማት እንዳትሰራ ግብፅ ለረጅም አመታት የምትከተላቸው 3ት ስትራተጂዎችና መፍትሔዎቻቸው!
#በታላቁ_መሪ_መለስ_ዜናዊ የተገለፀ!
" ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ዙርያ ልማት እንዳትሰራ ግብፅ ለረጅም አመታት 3 ስትራተጂዎችን በተቀናጀና በተሳካ ሁኔታ ስትተገብር ኖራለች። እነዚህ ስትራተጂዎች:-
#ስትራተጂ_አንድ ኢትዮጵያ ድሃ አገር ስለ ሆነች ካለ እርዳታና ብድር ውጭ በአባይ ወንዝ ዙርያ ትላልቅ ልማት መስራት አትችልም። ስለዚህ ግብፅ ያላትን Geo-politics advantage ተጠቅማ ኢትዮጵያ አባይን ለማልማት ማንኛውም እርዳታ እንዳታገኝ መስራት። ይህንን እስትራተጂ በብቃት ከመቶ አመት በላይ ሰርተው የተሳካላቸው ስትራተጂ ነው። አሁንም ቢሆን በዚህ ረገድ ስኬታማ የሆኑበት ስትራተጂ ነው።
#መፍትሔ የግብፅ ስትራተጂ አንድ ለመቋቋም ኢትዮጵያውያን አሁን ልንከተለው የሚገባ የመፍትሄ መንገድ በአባይ ወንዝ ላይ የልማት ስራዎች ለመስራት የይቻላል መንፈስ በማዳበር ካለ ብድርና እርዳታ ጠባቂነት በውስጥ አቅም የመጨረሻ ትልቁና ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሰለ ፕሮጀክት መገንባት።
#ስትራተጂ_ሁለት ግብፅ የአፍሪካ ግዙፍና በዘመናዊ ትጥቅ የተደራጀ ሰራዊት አስቀምጦ ማስፈራራት ነው። ይህንንም
#መፍትሔ ግብፅ ግዙፍና ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀ ሰራዊት ገንብታ ለዘመናት በጡንቿ ስታስፈራ ኑራለች። አሁን እኛ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ስትራተጂ ለመቋቋም ልንከተለው የሚገባን መንገድ #አለመፍራት ነው። አለመፍራት ሲባል እንዲሁ የጦርነት ቀረርቶ ማሰማት ሳይሆን እንደ አቅማችንም ቢሆን በሳይንሳዊ መንገድ የተጠና ዝግጅት ማድረግ ማለት ነው። አደጋው አስጊ አይደለም ግብፅ ኢ/ያን የመውረር አደጋ ትንሽ ነው። ቢሆንም ግን 5% አደጋም ቢሆን 5% ትኩረት ያስፈልገዋል።
#ስትራተጂ_ሦስት ግብፅ በ3ተኛ ደረጃ የምትከተለውና ውጤታማ የሆነ ስትራተጂ ግብፅ በውጭና በአገር ውስጥ ነጭ ለባሽ ተላላኪዎች በኩል የምትፈጥረው የማተራመስ አደጋ ነው። በዚህ ስትራተጂ ግብፅ በፈይናንስና በቁስ እየረዳች ኢትዮጵያውን እርሰ በርሳችን በምንፈጥረው ትርምስ ከልማት አጀንዳ ወጥተን በእርሰ በርስ ጦርነት ውስጥ እንድንጠመድ በማድረግ የተሳካ ስራዋን ስትሰራ ኖራለች።
#መፍትሔ 3ተኛው ስትራተጂ በጣም አደገኛ ስትራተጂ ነው። ከሁለቱም የመጀመርያዎቹ ስትራተጂዎች በላይ በአሁኑ ሰአት ለኛ አደገኛና ፈታኝ መንገድ ግብፆች ከውጭና ከውስጥ በነጭ ለባሽ ተላላኪዎቻቸው በኩል የሚፈጥሩብን የማተራመስ አደጋ ነው። ስለዚህ ይህንን አደገኛ ስትራተጂ ለመቋቋም እኛ ኢትዮጵያውያን ልንከተለው የሚገባን መንገድ ህዝበ፣ መንግስትና የፀጥታ ሃይሉ በቅንጅት ራሱ ከነጭ ለባሾች አደጋ የሚከላከልበት ስርአት መፍጠር ነው።"
#ታላቁ_መሪ_መለስ_ዜናዊ በአንድ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ላይ በአባይ ወንዝ ላይ የመንግስት ቁርጠኝነት ከገለፁበት ንግግር የተወሰደImage may contain: 2 people, sunglasses and outdoorበጋዜጠኛ ተኽለሃእማኖት ገብረመድህን

No comments:

Post a Comment

TEKLEHAIMANOT JOCO

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተያይዞ ዛሬ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ። በቃጠሎው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተመልክቷል። የዩኒቨርስቲው ...